ከጥር ወር ጀምሮ በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ22,800 በላይ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ እንደተያዙ እና ቢያንስ 622 ሰዎች በበሽታው እንደሞቱ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ከጥር ወር ጀምሮ በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ22,800 በላይ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ እንደተያዙ እና ቢያንስ 622 ሰዎች በበሽታው እንደሞቱ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል አስታወቀ ባሳለፈነው ሳምንት የበሽታው ስርጭት በ200% እንደጨመረ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ጂን ካሴያ በበይነ መረብ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኙ ማእከል እንደሆነች ተገልጿል። እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በብዛት ተጠቅተዋልም ተብሏል። በቅርብ ሳምንታት የሕክምና ተቋማት ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተያያዘ የተጠቁና የሞቱ ሰዎችን በሚመለከት የተለያየ መረጃ ሪፖርት እያደረጉ ሲሆን ይህ እየሆነ ያለው አንዳንድ ላቦራቶሪዎች በበሽታው እንደተያዙ የተረጋገጡ ሰዎችን ሲመዘግቡ ሌሎች የተጠረጠሩትንም ሪፖርት ስለሚያደርጉ ነው ተብሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0