በናይጄሪያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ባለፉት ሳምንታት 170 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ዘገባዎች አመለከቱ

ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ባለፉት ሳምንታት 170 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ዘገባዎች አመለከቱበሰሜናዊ ናይጄሪያ በሚገኙ አስር ግዛቶች በተከታታይ ቀናት በጣለ ዝናብ ሳቢያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በእርሻ መሬቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና የሀገሪቱን የምግብ እጥረት እንዳያባብስ ስጋት መፈጠሩን የምዕራቡ ዓለም ጋዜጣ ሰኞ እለት ዘግቧል። በተፈጥሮ አደጋው ከ200,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደተፈናቀሉ የገለጸው ዘገባው ሰሜን ናይጄሪያ በጎርፉ በክፉኛው እንደተጎዳች አክሏል። ጋዜጣው የናይጄሪያ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ባለስልጣን ቃል አቀባይ ማንዞ ኢዝኪዬል "በሚቀጥሉት ቀናት ማእከላዊ ክፍሎች እንዲሁም ወደታች ወረድ ብሎ ደቡባዊ ክፍሎችም ተመሳሳይ ጎርፍ ይገጥማቸዋል" ማለታቸውን ጠቅሶ አስነብቧል። በናይጄሪያ በቅርቡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 2,000 ሰዎች እንደተጎዱ እና ከ100,000 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት መውደሙን ዘገባው አክሎ ገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0