የቴሌግራም መስራች ዱሮቭ ክስ የሚመሰረትበት ከሆነ ፈረንሳይን ለቆ እንዳይወጣ ሊታገድ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል

ሰብስክራይብ
የቴሌግራም መስራች ዱሮቭ ክስ የሚመሰረትበት ከሆነ ፈረንሳይን ለቆ እንዳይወጣ ሊታገድ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል መርማሪዎች ከዱሮቭ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሊሞክሩ ወይም የእስር ጊዜውን በማራዘም ጫና ሊያደርጉበት እንደሚችሉ ፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ የፓሪስ ጠበቃን ጠቅሶ ዘግቧል። ዱሮቭ ላይ ክስ የሚቀርብ ከሆነ "ኗሪነቱ በውጭ ሀገር ከመሆኑ አንጻር ዳኛው ሊውስደው የሚችለው እርምጃ የሚጠበቅ ነው" ማለታቸውን የገለጸው ጋዜጣው የቁም እስር ሊጣልበት ወይም ከሀገር እንዳይወጣ ሊታገድ እንደሚችል አክለዋል። ዱሮቭ በፓሪስ ከተማ ዳርቻ በሚገኘው ብሔራዊ የፀረ-ማጭበርበር ክፍል ውስጥ በቁጥጥር ስር ሊሆን እንደሚችል ምንጮች ለአርአይኤ ኖቮስቲ ተናግረዋል። "ጉዳይ ለብሔራዊ ፀረ-ማጭበርበር ክፍል የተሰጠ መሆኑን ከግምት በማስገባት ዱሮቭ እዚያ ሊኖር ይችላል" ሲል ምንጩ ገልጿል። ፓቬል ዱሮቭ ታስሯል ተብሎ የታመነበት የማቆያ ስፍራ ፓሪስ ውስጥ በወንጀል ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች አቅራቢያ እንደሚገኝ ዘገባዎች አመላክተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0