ማክሮን የቴሌግራም ዋና መስሪያ ቤት ወደ ፓሪስ እንዲዛወር ለዱሮቭ በ2018 ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ታውቋል

ሰብስክራይብ
ማክሮን የቴሌግራም ዋና መስሪያ ቤት ወደ ፓሪስ እንዲዛወር ለዱሮቭ በ2018 ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ታውቋል ሆኖም የቴሌግራም መስራች ፓቬል ዱሮቭ ሃሳቡን ውድቅ አድርጎ እንደነበር ዎል ስትሪት ጆርናል ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ማክሮን ሃሳቡን ያቀረቡት የምሳ ግብዣ ላይ እንደነበርና ይህም ከዚህ በፊት እንዳልተዘገበ ምንጮቹ ተናግረዋል። የፈረንሳዩ መሪ በወቅቱ ለዱሮቭ የፈረንሳይ ዜግነት ስለመስጠት መወያየታቸውንም ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል። ማክሮን የዱሮቭ እስር ፖለቲካዊ እንዳልሆነ ገልፀው የስራ ፈጣሪው ጉዳይ በዳኞች እንደሚወሰን አረጋግጠዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0