የነሐሴ 22 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 22 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተሳተፉ 50 ግለሰቦችን ሶስት የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ በሞት ቅጣት እንዲቀጡ ጠይቋል። 🟠 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የሀገሪቱን የውሃ መሠረተ ልማት የሚያለማ እና የሚያስተዳድር እንዲሁም ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚስብ አዲስ ኤጀንሲ ለሟቋቋም የሚያስችል ህግ አጽድቀዋል። 🟠 ከያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ጀምሮ በአፍሪካ ሀገራት በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 22,800 ደርሷል። 🟠 የሩሲያ የአየር መቃወሚያ በቮሮኔዝ ክልል 8 እንዲሁም በሮስቶቭ ክልል 4 በአጠቃላይ 12 የዩክሬን ድሮኖችን በአንድ ጀምበር እንዳወደመ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 የዩክሬን ሚሳኤል በሩሲያ ኩርስክ ክልል ሰማይ ላይ መመታቱን የክልሉ ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ገለፁ። 🟠 ዘለንስኪ ቅሬታቸውን እየገለጹ ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ጦር የአሜሪካ የጦር መሳሪያዎችን ሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቆ መጠቀም እንዳይችሉ የተጣለውን እገዳ ለማንሳት እቅድ እንደሌለ ፔንታጎን አስታውቋል። 🟠 ዋሽንግተን በፖላንድ ለመጀመሪያ ግዜ የተገዙ ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶችን በመጪዎቹ ቀናት ወደ ዋርሶ ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኗን የፖላንድ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ገለፁ። 🟠 ትራምፕ ከሃሪስ ጋር ክርክር ለማካሄድ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ እና የክርክር መድረኩ ጳጉሜ 10 እንደሚካሄድ አስታወቁ። 🟠 ማክሮን በ2018 የቴሌግራም ዋና መስሪያ ቤትን ወደ ፓሪስ ለማዘዋወር ለዱሮቭ ሀሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም የመተግበሪያው መስራች ግን ሃሳቡን ውድቅ ማድረጉን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0