ቻድ ጥቅሟን ከሚያከብር ማንኛውም ሀገር ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አላማዬ ሀሊና ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ቻድ ጥቅሟን ከሚያከብር ማንኛውም ሀገር ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አላማዬ ሀሊና ተናገሩ ቻድ ከሞስኮ፣ ዋሽንግተን ወይስ ከፓሪስ ጋር ነው የምትሰለፈው ለሚለው የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ጥያቄ "የቻድ ፍላጎት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን እና የጋራ ጥቅምን በማክበር ላይ የተመሰረተ አጋርነትን ማስቀጠል ነው። ቻድ ጥቅሟን ከሚጠብቅ ማንኛውም ሀገር ጋር የትኛውንም ዓይነት ትብብር መፍጠር ትችላለች" ብለዋል። ሃሊና ከታሪካዊ እና ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ትብብርን ማስቀጠል ለቻድ በተለይም እንደ ሽብርተኝነት ያሉ ስጋቶችን ለመጋፈጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ቀደም ሲል የቻድ መከላከያ ሚኒስትር ሩሲያ ለአፍሪካ አስተማማኝ አጋር መሆኗን እንደገለጹ እና ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ በዋነኛነት ቻድን ለመበዝበዝ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል ሲል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0