የነሐሴ 21 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ባደረጉት ውይይት በኪዬቭ አገዛዝ እና በምዕራባውያን ደጋፊዎቹ የተያዘውን አጥፊ ፖሊሲ በተመለከተ ቁልፍ ግምገማ አድርገዋል። ፑቲን የሩሲያን የግጭት መፍችያ መፍትሄዎች ዘርዝረዋል። 🟠 ምዕራባውያን የዩክሬንን ግጭት መፍታት የሚፈልጉ ከሆነ ድርድር አስፈላጊ ነው ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገለጹ። 🟠 የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬን ጦር በኩርስክ ክልል ላይ ባደረሰው ጥቃት አሜሪካ ለነበራት ተሳትፎ ሩሲያ የምትሰጠው ምላሽ እስካሁን ከነበረው በእጅጉ የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። 🟠 የአውሮፓ ኮሚሽን ቴሌግራምን "በጣም ትልቅ የኦንላይን መድረክ" አድርጎ ስለማይመለከተው መተግበርያውን መቆጣጠር የእያንዳንዱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር ሃላፊነት እንጂ የብራሰልስ አይደለም ብሏል። 🟠 ዘለንስኪ ዩክሬን በ2024 መጨረሻ ከሩሲያ ጋር ያላትን የጋዝ ማስተላለፊያ ስምምነት እንደማታድስ አስታውቀዋል። 🟠 የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በኩርስክ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን የሚያሳይ ማስረጃ እንደቀረበላቸው የሮሳቶም ኃላፊ አሌክሲ ሊካቼቭ አስታውቀዋል። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በቅርቡ በቤጂንግ በሚያደርጉት ጉብኝት ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላትን የትብብር ደረጃ እንድትቀንስ ለማሳመን እንደሚሞክሩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ በሃማስ ተይዞ የነበረ ታጋች ማስለቀቁን አስታወቀ። ግለሰቡ መስከረም 26 ነበር የታገተው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የነሐሴ 21 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
የነሐሴ 21 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
Sputnik አፍሪካ
የነሐሴ 21 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ባደረጉት ውይይት በኪዬቭ አገዛዝ እና በምዕራባውያን ደጋፊዎቹ የተያዘውን አጥፊ ፖሊሲ በተመለከተ ቁልፍ ግምገማ አድርገዋል። ፑቲን የሩሲያን... 27.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-27T20:25+0300
2024-08-27T20:25+0300
2024-08-27T20:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий