ግብፅ ከጋዛ ሰርጥ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የእስራኤላውያን ወታደሮችን ይዞታ መቀጠል እንደምትቃወም ገልጻለች ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል

ሰብስክራይብ
ግብፅ ከጋዛ ሰርጥ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የእስራኤላውያን ወታደሮችን ይዞታ መቀጠል እንደምትቃወም ገልጻለች ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል በጋዛ የተኩስ አቁም ድርድር ቁልፍ አደራዳሪ የሆነችው ግብፅ በስትራቴጂካዊው የፊላዴልፊ መተላለፊያ የትኛውንም ዓይነት የእስራኤል ቆይታ እንደማትቀበል አስታውቃለች። የራፋ መሻገሪያን የሚያቅፈው እና ከእስራኤል ቀጥተኛ ቁጥጥር ውጪ ከፍልስጤም ግዛት ብቸኛ መውጪያ የሆነው ይህ መተላለፊያ የድርድሩ ዋና መከራከሪያ ነጥብ እንደሆነ እና የእስራኤል ኃይሎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ እየቀረበ ያለወ ጥሪ እየጨመረ እንደመጣ ታውቋል። ምንም እንኳን ዋሽንግተን የተወሰኑ ለውጦች እንዳሉ ብትገልጽም በኳታር፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ግብፅ አማካኝነት የሚደረጉ የሽምግልና ጥረቶች በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ማምጣታቸው አጠራጣሪ ሆኗል። የእስራኤል ጦር በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የፍልስጤምን የራፋ ማቋረጫ የተቆጣጥረ ሲሆን ወሳኝ የሆነውን የእርዳታ መስመር በመዝጋቱ ከግብፅ እና ከሌሎች ሀገራት ሰፊ ውግዘት ደርሶበታል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0