የማሊ ጦር በአልጄሪያ ድንበር አቅራቢያ 20 የሚሆኑ አሸባሪዎችን እንደደመሰሰ ተሰምቷል

ሰብስክራይብ
የማሊ ጦር በአልጄሪያ ድንበር አቅራቢያ 20 የሚሆኑ አሸባሪዎችን እንደደመሰሰ ተሰምቷል ወታደራዊ ዘመቻው በሀገሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ከአልጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በቲንዛኦዌተን ሰፈራ እንደተካሄደ የማሊ የዜና አውታር ማሊጄት የብሐራዊ የጦር መኮንንን ጠቅሶ ሰኞ እለት ዘግቧል። የመከላከያ ኃይሉ ባካሄደው የአየር ጥቃት አሸባሪዎችን ማጥፋት እንደቻለ የዜና አውታሩ ዘግቧል። የማሊ መከላከያ ኃይል የሀገሪቱን ህዝብ እና ንብረት በመላው ማሊ ለመጠበቅ ዝግጁ እንደሆነ አረጋግጧል ሲልም ማሊጄት ጨምሮ ገልጿል። የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ መንግሥት ሁሉንም ግዛት እንደሚቆጣጠር እና ጦሩ ቀሪ አሸባሪ እና ተገንጣይ ቡድኖችን እያጠቃ እንደሚገኝ ለስፑትኒክ በመጋቢት ወር ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0