የነሐሴ 21 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 21 ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያዎች በቤልጎሮድ ክልል ሶስት እንዲሁም በኩርስክ ክልል ሁለት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአንድ ምሽት እንደደመሰሱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 በስፑትኒክ እናት ኩባንያ ዋና አዘጋጅ ሲሞንያን ላይ የግድያ ሙከራዎችን በማቀነባበር የተከሰሱ በርካታ ተከሳሾች በከፊል ጥፋተኛ መሆናቸውን እንዳመኑ የክስ መዝገባቸው አሳይቷል። 🟠 የቴሌግራም መስራች ዱሮቭ የፈረንሳይ እስር እስከ ረቡዕ እንደተራዘመ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፈረንሳይ ለዜጋዋ ፓቬል ዱሮቭ አስቸኳይ የቆንስላ አገልግሎቶችን እንድታቀርብ መጠየቋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 የፈረንሳይ ህግ አስከባሪዎች የዱሮቭ ጠባቂ እና ረዳትን መመርመረው እንደለቀቁ ለነገሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ብራዚል፣ ኢንዶኔዥያ እና ደቡብ አፍሪካ የዩክሬን ግጭት መራዘም "የተወሰኑ የወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክሶች" ብዝበዛ ውጤት ነው ብለው ያምናሉ ሲሉ የቻይና መንግስት የዩሬዥያ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሊ ሁይ ተናግረዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ የተጠቀሱት ሀገራት የምዕራባውያን የጦር መሣሪያዎች ሩሲያ ላይ ጥቅም ላይ መዋላቸው ያሳስባቸዋል። 🟠 የፖላንድ ባለስልጣናት በዩክሬን ስለሚገኙት የፖላንድ ቅጥረኛ ወታደሮች ከማህበራዊ ትስስር ገጽ ወይም ከሞቱ በኋላ እንደሚያውቁ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0