ግራሚ አሸናፊው ራፐር ማክልሞር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን ጦርነት ላይ የምትጫወተውን ሚና በመቃወም የዱባይ ኮንሰርቱን ሰረዘ

ሰብስክራይብ
ግራሚ አሸናፊው ራፐር ማክልሞር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሱዳን ጦርነት ላይ የምትጫወተውን ሚና በመቃወም የዱባይ ኮንሰርቱን ሰረዘ ማክልሞር በጥቅምት ወር በዱባይ ሊያደርገው የነበረውን ኮንሰርት ዩኤኢ ለሱዳን አማፂ ቡድን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድጋፍ ትሰጣለች መባሉን በመጥቀስ ሰርዟል። ማክልሞር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ ዩኤኢ “የዘር ማጥፋት እና ሰብዓዊ ቀውስ” እየተፈጸመ ነው ብሎ እንደሚያምን በገለጸው ግጭት ለአርኤስኤፍ የምትሰጠውን ድጋፍ ካላቆመች ዩኤኢ ውስጥ ኮንሰርት ላለማካሄድ እንደሚገደድ ተናግሯል። "ይህ ምናልባት በአካባቢው የሚኖሩኝን የወደፊት ኮንሰርቶች አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል አውቃለሁ። ደጋፊዎቼንም ማስከፋት ደስ አይለኝም" ሲል ማክለሞር በትስስር ገጹ ላይ ጽፏል። “እኔም በጉጉት እየጠበቁት ነበር። ነገር ግን ዩኤኢ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ማስታጠቅ እና መደገፍ እስካላቆመች ድረስ ዝግጅቶቼን አላቀርብም" ብሏል። የራፐሩ ውሳኔ ዩኤኢ በግጭቱ ውስጥ ያላትን ሚና በተመለከተ በድጋሚ ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል። ዩኤኢ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን እንደማታስጥቅ ብትገልጽም የተመድ ባለሙያዎች እና የሱዳን መንግሥት የጦር መሳሪያዎች በቻድ በኩል ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተደጋጋሚ መላኩን የሚያሳይ ማስረጃዎች አቅርበዋል። የማክልሞር ኮንሰርት መሰረዝ በዱባይ የሙዚቃ ዝግጅት በሚያካሂዱ ሌሎች አርቲስቶች መካከል ክርክር አስነስቷል። "በዩኤኢ ውስጥ ሌሎች አርቲስቶች ስለሚያካሂዱት ኮንሰርት ምንም አይነት አስተያየተ የለኝም። ነገር ግን በዱባይ ስራዎቻቸውን ለማቅረብ ለተዘጋጁ የሙያ እኩዮቼ ጥያቄ አለኝ። መድረኮቻችንን ተጠቅመን የጋራ ነፃነትን ማነቃነቅ ከቻልን፤ ምን ያህል ማሳካት እንችላለን?” ሲል ራፐሩ ጽፏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0