ኬንያ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮን ለመደገፍ ወታደሮቿን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ አሰማራች

ሰብስክራይብ
ኬንያ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮን ለመደገፍ ወታደሮቿን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ አሰማራች የኬንያ ፈጣን ምላሽ ኃይል (KENQRF 4) አራተኛው ክፍለ ጦር የመጀመርያው ቡድን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቅንቷል። ወታደሮቹ ታጣቂ ቡድኖችን በመዋጋት፣ ሲቪሎችን በመጠበቅ፣ ሰብዓዊ እርዳታዎችን በመደገፍ እና የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈታት እና መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ በተለያዩ ስራዎች ላይ እንደሚሰማሩ የኬንያ መከላከያ ኃይል በመግለጫው አስታውቋል። ኃይሉ በታጣቂ ቡድኖች የሚታመሱትን ምስራቃዊ ግዛቶች የማረጋጋት ተልዕኮ ከተሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ጋር ይቀላቀላል። “ወታደሮቻችን ቀጣይ ግዴታቸውን ለመወጣት ተዘጋጅተዋል። ተልእኮውን በብቃት ለመወጣት ጥብቅ ስልጠና ወስደዋል እንዲሁም አስፈላጊ ክህሎቶችን ታጥቀዋል። በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ ነን" ሲሉ የኬንያ ሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሲሞን ሴዳ ተናግረዋል። እሁድ እለት በሰሜን ኪቩ ግዛት ሉቤሮ ወረዳ በኮንጎ ጦር እና በኤም 23 አማፂ ቡድን መካከል ከባድ ውጊያ በድጋሚ እንደተነሳ ተሰምቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0