ዩክሬን በኩርስክ ክልል ከ400 በላይ ወታደሮች እና 27 የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ቀን ውስጥ እንዳጣች የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል

ሰብስክራይብ
ዩክሬን በኩርስክ ክልል ከ400 በላይ ወታደሮች እና 27 የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ቀን ውስጥ እንዳጣች የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል የሚኒስቴሩ ተጨማሪ መግለጫዎች፦🟠 የዩክሬን መከላከያ ኃይል በኩርስክ አቅጣጫ ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ6,200 በላይ ወታደሮችን እና 73 ታንኮችን አጥቷል። 🟠 የሩሲያ ሰራዊት ኩርስክ ክልል ውስጥ በክሬሚያኖዬ፣ ማላያ ሎክንያ እና ኔቻዬቭ አቅጣጫ ጥቃቶችን መክቷል። 🟠 ኩርስክ አቅራቢያ በኮማሮቭካ፣ ስፓልኖዬ፣ ኮሬኔቮ፣ ፖግሬብኪ እና ኦልጎቭካ አቅጣጫ ለማጥቃት የተደረጉ ሙከራዎች ከሽፈው የዩክሬን ጦር 30 የሚደርሱ ወታደሮችን በሞት እና ጉዳት አጥቷል። 🟠 የሩሲያ ጦር የዩክሬን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስን በሚደግፉ ወሳኝ የኢነርጂ መሠረተ ልማት ተቋማት ላይ በአልሞ ተኳሽ የጦር መሳሪያዎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከፍተኛ ጥቃት አካሂዷል። 🟠 የሩሲያ "ዩግ" (ደቡብ) ኃይሎች ቡድን በ24 ሰዓት ውስጥ የበለጠ ምቹ ቦታዎችን የተቆጣጠረ ሲሆን ጠላት 570 የሚደርሱ የጦር ሰራዊት አባላት፣ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና አራት የመስክ ጥይት መጋዘኖችን አጥቷል። 🟠 የዩክሬን ጦር ኃይል በካርኮቭ እና ሱሚ ክልሎች በሩሲያ "ሴቨር" (ሰሜን) ቡድን ኃይሎች የዘመቻ አካባቢ በአንድ ቀን ውስጥ 90 የሚደርሱ ወታደሮችን አጥቷል። 🟠 የሩሲያ "ሰንትር" (ማእከል) ቡድን ኃይሎች የዩክሬን ጦር ኃይሎችን ሰባት የመልሶ ማጥቃት በአንድ ቀን በመመከት ጠላት 585 የሚደርሱ ወታደሮችን፣ ሶስት ታንኮችን፣ አንድ ማርደር የእግረኛ ተዋጊ ተሽከርካሪ እና አንድ የወታደሮች ተሸካሚ ተሽከርካሪን አጥቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0