ሩሲያ የቴሌግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዱሮቭ እስርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ምላሾችን እንደምትከታተል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ የቴሌግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዱሮቭ እስርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ምላሾችን እንደምትከታተል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ "በሌሎች ጉዳዮች በሀገራችንና ስራዎቻችን ላይ ፖለቲካዊ፣ የመረጃ እና ስነ-ልቦናዊ ጫና የሚያሳድሩትን የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ባህሪ እና ምላሽ እንከታተላለን። የሰብዓዊ መብቶችን እና የመናገር ነጻነትን ለመጠበቅ የሚያሳዩትን ቁርጠኝነት ማየትና እንፈልጋለን" ሲሉ ማሪያ ዛካሮቫ ለሮሲያ ​​24 ብሮድካስቲንግ ተናግረዋል። የዱሮቭ እስር ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ሞስኮ ወደ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ትዞር እንደሆነ ሲጠየቁ ዛካሮቫ ጠበቆቹ አስፈላጊዎቹን እርምጃዎች መወያየት ይኖርባቸዋል ብለዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0