በኮንጎ ሪፐብሊክ 21 ሰዎች በኤምፖክስ መያዛቸው ተረጋገጠ

ሰብስክራይብ
በኮንጎ ሪፐብሊክ 21 ሰዎች በኤምፖክስ መያዛቸው ተረጋገጠ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት 158 የተጠረጠሩ ሰዎች እንደነበሩ እና ባሳለፍነው ሐሙስ የተረጋገጡትን ሁለት ሰዎች ጨምሮ በቫይረሱ የተያዙ 21 ሰዎች መመዝገባቸውን የጤና ሚኒስትሩ ጊልበርት ሞኮኪ እሁድ ዕለት በመንግስት ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት የኤምፖክስ ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ ነሐሴ 7 ቀን በሽታው የህብረተሰብ ጤና አደጋ መሆኑን አስታውቋል። በዚህ ዓመት በ18 የአፍሪካ ሀገራት ወደ 40,000 የሚጠጉ በኤምፖክስ የተያዙ ሰዎች እና ከ1,400 በላይ ሞት ተመዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የተከሰተውን የኤምፖክስ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት ነው ሲል ነሐሴ 9 ቀን አውጇል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0