ሄዝቦላ በመጀመሪያ አፀፋዊ ምላሹ እስራኤል ውስጥ 11 ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደመታ አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ሄዝቦላ በመጀመሪያ አፀፋዊ ምላሹ እስራኤል ውስጥ 11 ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደመታ አስታወቀ "የመጀመሪያው ደረጃ ሙሉ በሙሉ የተሳካ ነበር። ይህ በእስራኤል ይዞታዎች እና ምሽጎች ላይ የደረሰው ጥቃት፤ ድሮኖች እስራኤል ውስጥ ወደሚገኙ ዋና ኢላማዎች እንዲበሩ ለማረጋገጥ የተካሄደ ነበር። ድሮኖቹ በእቅዱ መሰረት በረዋል" ሲል የንቅናቄው የፕሬስ አገልግሎት ገልጿል። ዒላማዎቹ ሶስት የእስራኤል መከላከያ ኃይል የጦር ሰፈሮች፣ በጎላን ተራሮች የሚገኙ ሁለት የጦር ሰፈሮች፣ ሶስት ምሽጎች እና በርካታ ይዞታዎችን ያካትታሉ። ሄዝቦላ እስራኤል በቤይሩት ከተማ መኖሪያ ሰፈሮች ላደረሰችው ጥቃት እና ለኮማንደር ፉአድ ሹክር ግድያ አጸፋዊ ምላሽ መጀመሩን ቀደም ብሎ እሑድ እለት አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0