በማሌዥያ ማእከላዊ ኩዋላ ላምፑር የእግረኛ መንገድ ተደርምሶ አንድ ቱሪስት 8 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ገብታ ደብዛዋ ተጠፍቷል

ሰብስክራይብ
  በማሌዥያ ማእከላዊ ኩዋላ ላምፑር የእግረኛ መንገድ ተደርምሶ አንድ ቱሪስት 8 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ገብታ ደብዛዋ ተጠፍቷልየአካባቢው ፖሊስ አዛዥ የአይን እማኞች ዋቢ አድረገው እንደተናገሩት ሴትየዋ በእግረኛ መንገድ ላይ ስትሄድ በድንገት መሬቱ ተደርምሶ እንደወደቀች ተናገረዋል። ፖሊስ ከመሬት በታች ባለው የውሃ መውረጃ ትቦ ውስጥ በመግባቷ ወራጅ ውሃ ሊወስዳት እንደሚችል ጠርጥሯል። የአሰሳ እና የህይወት አድን ተግባሩ እየተሰራ ነው።ተጎጂዋ የ48 ዓመቷ ህንዳዊ ቱሪስት ስትሆን ከባለቤቷ እና ከጓደኞቿ ጋር በማሌዥያ የእረፍት ጊዜዋን እያሳለፈች ነበር። የኩዋላ ላምፑር ፖሊስ አዛዥ እንደተናገሩት ተሪስቶቹ ከሁለት ወራት በፊት ማሌዥያ የገቡ ሲሆን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ቀጠሮ ይዘው ነበር።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0