የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ የሚያስችሉ መንገዶችን ለመክፈት ተስማሙ

ሰብስክራይብ
የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ የሚያስችሉ መንገዶችን ለመክፈት ተስማሙየሱዳን ታጣቂ ሃይሎች እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች (RSF) በሁለት መንገዶች ሰብአዊ እርዳታን ለማድረስ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፤ በዳርፉር በስተምዕራብ በሚገኘው አድሬ ድንበር እና በዳባ ​​መስመር ፖርት ሱዳንን ከሰሜን እና ምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች ጋር የሚያገናኘው መስመር። ይህ ውሳኔ በሱዳን ቀውስ ዙሪያ ለተከታታይ 10 ቀናት በጄኔቫ የተካሄደው ድርድር ውጤት ነው።በዳርፉር ለሚገኙ  የተራቡ ዜጎች የሚሆን ሰብዓዊ ርዳታ የጫኑ መኪኖች ወደ ሥፍራው እየተጓዙ መሆናቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።እ.አ.አ ከነሀሴ 14 ጀምሮ በሱዳን የሰብአዊ አቅርቦትን ለማሻሻል ያለመ ውይይት በጄኔቭ ተካሂዷል ። በውይይቱ ላይ ከግብፅ፣ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ከስዊዘርላንድ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑካን አባላት ተሳትፈዋል። ሁለቱም የግጭቱ ተዋንያኖች የተጋበዙ ቢሆንም የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ብቻ ልዑኩን ልከዋል። በውይይቱ ላይ የሱዳን ታጣቂ ሃይሎች በአካል ያልተገኙ ሲሆን በሩቁ ሆነው ግን ተሳትፈዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0