በማዕከላዊ ናይጄሪያ በደረሰ አሳዛኝ ጥቃት 13 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ እሮብ እለት በቦኮ ሃራም ታጣቂዎች የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም በተባለ አሰቃቂ ጥቃት ፤ በሺሮ ወረዳ አንጉዋን ማይ-ጊሮ ማህበረሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሴቶችን ጨምሮ 13 ገበሬዎች ተገድለዋል። ታጣቂዎቹ በሞተር ሳይክሎች መጥተው የግብርና ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የፈፀሙ ሲሆን አብዛኞቹ ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመትተዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የጸጥታ ምንጮችን ጠቅሰው የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።የኒጀር ግዛት ተጠባባቂ ገዥ የሆኑት ያኩቡ ጋርባ በፀጥታ አካላት ላይ ጥልቅ ምርመራ እንደሚካሄድ አረጋግጠዋል።በተጨማሪም ተጎጂዎቹ ለማዕድን ፍለጋ እንደሚሄዱ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የተሳሳተ መሆኑን ገልፀው፤ ተጎጂዎቹ በእውነቱ በተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የነበሩ እና ወደ አንጉዋን ማይ-ጌሮ ለእርሻ ስራ ለመሄድ የተዘጋጁ መሆናቸውን አብራርተዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በማዕከላዊ ናይጄሪያ በደረሰ አሳዛኝ ጥቃት 13 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ
በማዕከላዊ ናይጄሪያ በደረሰ አሳዛኝ ጥቃት 13 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ
Sputnik አፍሪካ
በማዕከላዊ ናይጄሪያ በደረሰ አሳዛኝ ጥቃት 13 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ እሮብ እለት በቦኮ ሃራም ታጣቂዎች የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም በተባለ አሰቃቂ ጥቃት ፤ በሺሮ ወረዳ አንጉዋን ማይ-ጊሮ ማህበረሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሴቶችን ጨምሮ 13 ገበሬዎች... 23.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-23T19:57+0300
2024-08-23T19:57+0300
2024-08-23T20:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий