ቻይና እና ቤላሩስ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብርን ሊያጠናክሩ ነው

ሰብስክራይብ
ቻይና እና ቤላሩስ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብርን ሊያጠናክሩ ነው“ሁለቱ ወገኖች በመከላከያ፣ በፍትህ፣ በህግ ማስከበር እና በፀጥታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ያጠናክራሉ” ሲል በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ ታትሞ በወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል። ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ባለሙያዎችን በማሰልጠን፣ የሳይበር እና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በጋራ ለመዋጋት እንዲሁም ሽብርተኝነትን፣ ጽንፈኝነትን እና ተገንጣይ ኃይሎችን በመዋጋት ረገድ ያላቸውን ትብብር ያጠናክራሉ ብሏል።"ሁለቱ ወገኖች ህገ-ወጥ የአንድ ወገን የማስገደድ እርምጃዎችን እንደሚያወግዙ እና እንደዚህ አይነት እርምጃዎች የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጥሱ ብቻ ሳይሆን የ 2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ አግባብነት ያላቸውን ውሳኔዎች ይቃረናል ብለው አንደሚያምኑ " በመግለጫው ተገልጿል።ሁለቱ ሀገራት አዲስ አይነት አለም አቀፍ ግንኙነት ለመገንባት እና በእኩል እና በስርዓት የሚመራ የብዝሃ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲኖር በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0