በቦትስዋና ታሪካዊ የተባለ የአልማዝ ማዕድን አገኘት

ሰብስክራይብ
በቦትስዋና ታሪካዊ የተባለ የአልማዝ ማዕድን አገኘትበሉካራ ዳይመንድ ኮርፖሬሽን 2,492 ካራት መጠን ያለው አልማዝ በቦትስዋና ካሮዌ ማዕድን ሥፍራ ማግኘቱ ይታወሳል። ይህ ግዙፍ ዕንቁ ከ120 ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ የተገኘውን ባለ 3,106 ካራት ኩሊናን አልማዝ በመከተል ሁለተኛው ትልቁ አልማዝ ነው።የአልማዝ ጥራት ገና ሙሉ በሙሉ ባይገመገምም፤ የአልማዙ ትልቅነት ለሉካራ ትልቅ ድል ነው የተባለ ሲሆን ግኝቱ ሊሳካ የቻለው በካሮዌ የላቀ የራጅ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሲሆን ይህም ግዙፍ እንቁዎችን በመለየት በኢንዱስትሪው ውስጥ ትልቅ ፈተና ያስቀረ ነው። "እንዲህ ያለውን ግዙፍና ከፍተኛ ጥራት ያለው ድንጋይ ሳይነካ ማግኘት መቻል የአልማዝ ፍለጋ ዘዴያችንን ውጤታማነት ያሳያል" ሲሉ የሉካራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊልያም ላም በሰጡት መግለጫ የዚህን ግኝት አስፈላጊነት አጉልተው ተናግረዋል። እስካሁን በትልቅነቱ የተመዘገበው የኩሊናን አልማዝ የተለያዩ መጠን ያላቸው የተንቆጠቆጡ እንቁዎች የተቆረጠ ሲሆን ከነዚህም መካከል ታላቁ የአፍሪካ ኮከብ እና የአፍሪካ ትንሹ ኮከብ አሁን የብሪታንያ ዘውድ ጌጣጌጦችን አስውቦ ይገኛል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0