የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አንድ የጋራ ገንዘብ እንዲኖር ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ አሻሽሏል

ሰብስክራይብ
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አንድ የጋራ ገንዘብ እንዲኖር ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ አሻሽሏልየምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) አንድ የጋራ የገንዘብ ምንዛሪ እንዲኖር ለማድረግ ያሰበበትን የጊዜ ሰሌዳ ላይ ማሻሻያ አድርጓል፤ አሁን ኢላማ ያደረገው ቀደም ሲል ከታቀደው 2024 ይልቅ 2031 ነው። ይህን ማሻሻያ የኢኤሲ ዋና ፀሃፊ ቬሮኒካ ሙኒ ንዱቫ በቅርቡ ከምስራቅ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ጋር በነበረው የክብ ጠረጴዛ ውይይት ወቅት ተናግረዋል። " በጋራ ገንዘብ ፍኖተ ካርታ መሰረት የገንዘብ ዩኒየኑ በ2024 ይቋቋማል ተብሎ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም ፤  ተግባራዊ ባለመሆኑ የጊዜ ሰሌዳው ወደ 2031 ተሻሽሏል" ስትል ተናግራለች።ምንም እንኳን መዘግየቶች ቢኖሩም በተለያዩ መስኮች መሻሻል ታይቷል፤ ይህም የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት እና በቀጠናው ውስጥ የምንዛሪ መለዋወጥን የሚያመቻች የምስራቅ አፍሪካ የክፍያ ስርዓት መመስረትን ጨምሮ ሥራዎች ተሰርተዋል።ሆኖም አንዳንድ ተግዳሮቶች አሉ፤ ለምሳሌ የምስራቅ አፍሪካ የገንዘብ ተቋምን መቀመጫን መወሰን እና ቁልፍ የሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ መስፈርቶችን ማሟላት. እንዲሁም የዋጋ ግሽበትን እና የገንዘብ ጉድለት የሚመለከቱ ጉዳዮች እንደሆኑ ተገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0