ኒጀር ተቋርጦ በነበረው በቤኒን በኩል የነዳጅ ዘይት መላክ ጀመረች

ሰብስክራይብ
ኒጀር ተቋርጦ በነበረው በቤኒን በኩል የነዳጅ ዘይት መላክ ጀመረች ኒጀር በቤኒን በኩል የነዳጅ ዘይት ምርቷን ወደ ውጪ መላክ ለጊዜው እንዲቆም ተደርጎ ነበረ። ወደ ውጪ መላክ የቆመው ኒጀር ከቤኒን የሚገቡ ሸቀጦች ላይ የተጣለችውን እገዳ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ሲሆን፤ ቤኒን በቻይና የገንዘብ ድጋፍ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የባህር ዳርቻ በተዘረጋው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ አማካኝነት ወደ ውጭ መላክ እንዳትችል አድርጋ ነበር። በምላሹም ኒጀር በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የቧንቧ መስመሩን ዘግታለች፤ ይህም የሆነው ተወካዮቿ በወደቡ ላይ የነዳጅ ጭነቶችን ሲቆጣጠሩ በቤኒን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው።የምዕራብ አፍሪካ የጋዝ መስመር ኩባንያ ወኪል ለምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን እንዳረጋገጠው አውራ ኤም የተባለ የላይቤሪያ ባንዲራ ያነገበው ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ማክሰኞ ከቤኒን ወደብ አንድ ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ መጫኗ ተዘግቧል። የባህር ትራፊክ የመርከብ ክትትል መረጃ እንደሚያሳየው መርከቧ ወደ ቻይና ቲያንጂን ነው ያመራቸው።ውዝግቡ እንዴት እንደተፈታ ግልጽ ባይሆንም ወደ ውጭ የተላከው ዘይት እንደገና መጀመሩ ጠቃሚ እድገትን ያሳያል።ምስሉ ከባህር ትራፊክ ድረ-ገጽ የተገኘ ነው።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0