የዩክሬን መንግስት በያዝነው የበልግ ወቅት ከሩሲያ ጋር የሰላም ውይይት ለማድረግ ማቀዱን ዘገባዎች አመልክተዋል

ሰብስክራይብ
የዩክሬን መንግስት በያዝነው የበልግ ወቅት ከሩሲያ ጋር የሰላም ውይይት ለማድረግ ማቀዱን ዘገባዎች አመልክተዋልየኪየቭ መንግስት ከሞስኮ ጋር ለሁሉም የሚስማማ የእስረኞች ልውውጥ፣ የምግብ ዋስትና እና የኒውክሌር ደህንነት ጉዳይ ዙሪያ እንደሚወያይ ይጠበቃል ሲል የኪየቭ ኢንዲፔንደንት የዜና ፖርታል የዩክሬኑን መሪ ዘሌንስኪን ምንጭ ጠቅሶ ዘግቧል። ቀደም ሲል የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ በኩርስክ ክልል ከተፈፀመው የሽብር ድርጊት በኋላ ጠላት ሙሉ በሙሉ እስኪሸነፍ ድረስ ከኪየቭ ጋር ምንም አይነት ድርድር እንደማይኖር መናገራቸው ይታወሳል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0