ሞስኮ የምዕራቡ ዓለም ለወረሰባት ሀብትና ንብረት አፅፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ሞስኮ የምዕራቡ ዓለም ለወረሰባት ሀብትና ንብረት አፅፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀእ.አ.አ በሀምሌ ወር መጨረሻ ብራሰልስ የመጀመሪያውን ወታደራዊ ዕርዳታ ወደ ዩክሬን ልኳል። ይህም 1.5 ቢሊዮን ዩሮ የሚገመት የማይንቀሳቀስ የሩሲያ ሀብትና ንብረት ነው። "የአጸፋ እርምጃዎች በእርግጠኝነት ይኖራሉ። እርምጃዎቹ ሚዛናዊ፣ የተረጋገጡ እና በሩሲያ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ላይ ጉዳት የማያስከትሉ ናቸው፤ በሩሲያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲሁም ወርቅ ላይ  'እጃቸውን ለመጫን' በሚሞክሩት ላይ ሩሲያ በቂ የሆነ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች ለመውስድ የሚያስችል ዝግጅት አድርጋለች" ሲሉ ሚኒስቴሩ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።ከዚህም በላይ የተያዙ የሩሲያ ንብረቶች ገቢን ወደ ዩክሬን መላክ ሕገወጥ ነው ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ገልጿል።በተጨማሪም ንብረቶችን እንዳይንቀሳቀሱ የማገድ ልማድ ዩሮን እንደ መጠባበቂያ ገንዘብ መጠቀም ላይ ያለውን አመለካከት ሊቀነስ ይችላል ብሏል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0