የሳህል ህብረት ሀገራት በዩክሬን ላይ የሚስገቡትን ደብዳቤ ለአባል ሀገራቱ ለማጋራት እየጠበቀ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ተናግረዋል

ሰብስክራይብ
  የሳህል ህብረት ሀገራት በዩክሬን ላይ የሚስገቡትን ደብዳቤ ለአባል ሀገራቱ ለማጋራት እየጠበቀ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ተናግረዋል  የቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ቋሚ መልእክተኞች ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ዩክሬን በሳህል ቀጠና ለሽብርተኞች ድጋፍ በማድረጓ እርምጃ እንዲወስድባት የሚጠይቅ የጋራ ደብዳቤ ማሰነዳታቸውን ስፑትኒክ ያገኘው መረጃ ያሳያል። "ደብዳቤው እስካሁን አልደረሰም፤ እንደአስፈላጊነቱ ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት ይጋራል። መልእክታችን የሳህልን ቀጠና መረጋጋት ለማስፈን ሁሉም እንዲረባረብ የሚያበረታታ ነው፤ ​​ይህም በንቃት የተሳተፍንበት ጉዳይ ነው" ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድረጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በኪየቭ ተሳትፎ ላይ አስተያየት ሳይሰጡ ተናግረዋል።እ.ኤ.አ ነሐሴ 6 ኒጀር ኪየቭ በማሊ ላይ ባደረገችው ጥቃት ምክንያት ከዩክሬን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች። የማሊ ጊዚያዊ መንግስት ከዩክሬን ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሁ ማቋረጡን አስታውቋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0