ሩሲያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገለጸችበኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን የተመራ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያዎች ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን የጎበኙ ሲሆን፤ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ(ዶ/ር) በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን በሚመለከት ገለጻ አድርገውላቸዋል። "ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርምርና ትግበራ የሚበረታታ ሥራ መስራቷን ከጉብኝቱ ተረድተናል " ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡በተለይም ቴክኖሎጂና ዘመናዊነትን የእድገት መሠረት ለማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባላቸው ፍላጎት በርካታ ለውጦች በአጭር ጊዜ ውስጥ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ኢትዮጵያ ዘርፉን አጠናክራ ለማስቀጠል በምታደርገው ጥረት ሩሲያ ያላትን ልምድ ከማካፈል ጀምሮ በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0