በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ 20 ሰዎች መሞታቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል

ሰብስክራይብ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ 20 ሰዎች መሞታቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል' ጂሰስ ክራይስት ' የተባለችው ጀልባ 300 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ በሉኪ ወንዝ ላይ በመጓዝ ላይ ሳለች በቁርጥራጭ እንጨቶች ጋር በመላተሟ ሰኞ ሌሊት ሰጥማለች። የአካባቢው ባለስልጣናት ቀደም ሲል 43 ሰዎች በህይወት መገኘታቸውን እንዲሁም የሶስት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን አረጋግጠዋል። አስከሬኖቹ በሜይ-ንዶምቤ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ማድጆኮ መንደር አቅራቢያ መገኘቱን አክቱዋላይት የዜና አውታር ዘግቧል። ጀልባው 300 ሰዎችን ለማጓጓዝ የሚያስችል አለመሆኑ ለመስጠሟ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል። ቀደም ሲል የወጡ ዘገባዎችም ድርጊቱን ተከትሎ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች መጥፋታቸውን ገልጸዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0