አልጄሪያ በጎርፍ ለተጎዱ የኒጀር ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ ለገሰች

ሰብስክራይብ
አልጄሪያ በጎርፍ ለተጎዱ የኒጀር ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ ለገሰችእ.አ.አ ነሃሴ 19 ከአልጄሪያው ቡፋሪክ አየር ሃይል ማረፊያ ወደ ኒያሚ አውሮፕላን አየር ማረፊያ እርዳታ የጫኑ 4 የጦር አውሮፕላኖች ወደ ኒጀር ማቅናታቸውን የአልጄሪያ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።በአልጄሪያ ቀይ ጨረቃ የተለገሱ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም ድንኳን እና ፍራሾች ይገኙበታል።እርምጃው በቅርቡ በኒጀር የጎርፍ አደጋ ያስከተለውን ውድመት” ተከትሎ፤ “ከወንድማማች እና ወዳጃዊ ሀገራት ጋር ያለውን የትብብር መርህ መሠረት አድርጎ የተለገሰ መሆኑ ተገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0