የኳታር አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካው ኤርሊንክ አየር መንገድ 25 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የኳታር አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካው ኤርሊንክ አየር መንገድ 25 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታወቀ "የኳታር አየር መንገድ ግሩፕ ከደቡብ አፍሪካው ፕሪሚየር ክልላዊ አየር መንገድ-ኤርሊንክ 25% ድርሻ አግኝቷል። ይህ የተነገረው የባለብዙ ሽልማት አሸናፊ የሆነው የኳታር አየር መንገድ በአፍሪካ አህጉር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የበለጠ ለማሳደግ ያለውን ፍላጎት ተከትሎ ነው" ሲል ኩባንያው ማክሰኞ እለት በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል። ኤርሊንክ ወደ 15 የአፍሪካ ሀገራት ከ45 በላይ በረራዎችን ያደርጋል ሲል መግለጫው የገለፀ ሲሆን፥ የአየር መንገዱ ከ65 በላይ አውሮፕላኖችን ያሉት መሆኑንም አስታውቋል።የተቆጣጠሪ መሥሪያ ቤቱን ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ በመሆኑ አሁን ላይ የስምምነቱ ዋጋ መግለፅ እንዳልተቻለ ተገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0