የኬንያ አየር መንገድ በመጀመርያው ግማሽ አመት 4 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ትርፍ በማግኘት ከአስር አመታት በላይ የቆየውን የኪሳራ ጉዞው ገትቷል

ሰብስክራይብ
የኬንያ አየር መንገድ በመጀመርያው ግማሽ አመት 4 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ትርፍ በማግኘት ከአስር አመታት በላይ የቆየውን የኪሳራ ጉዞው ገትቷልየተሳፋሪዎች ቁጥር መጨመር፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መገታት እና የኬንያ መገበያያ ገንዘብ ጠንካራ መሆን ለአየር መንገዱ ትርፋማነት በምክንያትነት ተጠቅሷል።ወረርሽኙ በአለም አቀፍ ጉዞ ላይ ያስከተለው አስከፊ ጉዳት፣ ከኬንያ ሽልንግ ከፍተኛ የዋጋ ቅነሳ እና የወለድ ምጣኔ መጨመር ጋር ተዳምሮ አየር መንገዱን ወደ ኪሳራ አፋፍ ገፍቶት ነበር።የኩባንያው የመጀመርያው የግማሽ ዓመት ትርፍ 513 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ( 4 ሚሊዮን ዶላር ገደማ) ሲሆን ይህም ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የኬንያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አላን ኪላቩካ አየር መንገዱ ዘላቂ እድገትን እና የፋይናንስ መረጋጋትን ለማስፈን አዎንታዊ ሁኔታዎት መኖራቸውን ተናግረዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0