የነሐሴ 14 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ፑቲን ቬሴቮሎድ ትካቼንኮን በኬንያ አዲስ አምባሳደር እና በናይሮቢ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቋሚ ተወካይ አድርገው ሾሙ። 🟠 በሩሲያ እና የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር እና ለአፍሪካ ሀገራት ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሞስኮ በተከበረው ዓመታዊው የሳድክ ቀን ገልጿል። 🟠 ሩሲያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ግቧን እንዳሳካች ሁሉ ኒዮ ናዚዎችን በመዋጋት ግቧን ታሳካለች ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል 🟠 ፑቲን በቤስላን የሽብር ጥቃት ሰለባ ከነበሩት የተጎጂዎች እናቶች ጋር ተገናኙ። 🟠 በጀርመን እና ፖላንድ መካከል ያለው ግንኙነት በኖርድ ስትሪም ቧንቧዎች ላይ በተደረገው ምርመራ ምክንያት መበላሸቱን የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ባኩ ለብሪክስ አባልነት በይፋ እንዳመለከተች የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። 🟠 የአሜሪካ የግል ወታደራዊ ኩባንያዎች የዩክሬን ጦር ወደ ሩሲያ ኩርስክ ግዛት ዘልቆ በመግባት ባካሄደው ጥቃት ውስጥ ተሳትፎ እንዳላቸው የሚያሳዩ ማስረጃዎች ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ግጭት ተሳትፎ እንዳላት የሚያረጋግጥ ነው ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ 🟠 የብራዚል ባለስልጣናት ለዋትስአፕ አማራጭ የሚሆን ብሔራዊ መልእክት መላላኪያ መተግበርያ ለማዘጋጀት ወሰኑ። 🟠 የዓለም ጤና ድርጅት ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተገናኘ በተከሰተው የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምክንያት የፊት ጭንብል ማድረግ እንደማይመክር አስታወቀ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የነሐሴ 14 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
የነሐሴ 14 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
Sputnik አፍሪካ
የነሐሴ 14 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ፑቲን ቬሴቮሎድ ትካቼንኮን በኬንያ አዲስ አምባሳደር እና በናይሮቢ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቋሚ ተወካይ አድርገው ሾሙ። 🟠 በሩሲያ እና የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) መካከል ያለውን ግንኙነት... 20.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-20T20:55+0300
2024-08-20T20:55+0300
2024-08-20T21:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий