ዘለንስኪ ዩክሬናውያን በከፍተኛ ቁጥር ከሀገር እየወጡ እንደሆነ ተቀበሉ

ሰብስክራይብ
ዘለንስኪ ዩክሬናውያን በከፍተኛ ቁጥር ከሀገር እየወጡ እንደሆነ ተቀበሉ ከዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ንግግር "ከዚህ በፊት ይህን ያህል ህዝብ ከሀገር ውጭ ኖሮን አያውቅም፤ በሚሊዮኖች ስለሚቆጠሩ ዩክሬናውያን ነው የምናወራው" ብለዋል። ሀገሪቱን ለቀው የወጡ ዜጎች "በሩሲያ ፕሮፓጋንዳ ተጽእኖ ውስጥ" እንደሆኑ እና ከሀገራቸው ጋር የነበራቸውን የባህል ግንኙነት እንደተነፈጉ ተናግረዋል። ሀገሪቱን ለቀው በወጡ የዩክሬን ዜጎች ላይ የሩሲያን ተጽእኖ ለመከላከል የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አንዳንድ ተግባራት የሚረከብ አዲስ ሚኒስቴር እንደሚቋቋም ዘለንስኪ ጨምረው ገልጸዋል። "በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦቻችን በሌሎች ሀገራት ይገኛሉ። ከዩክሬን ጋር ያላቸው ዝምድና እና ግንኙነት፣ እንደ ሀገር ጥቅማችንን ማስጠበቅ - ይህ ሁሉ የአዲሱ ተቋም ኃላፊነት ይሆናል" ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0