ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የድጋፍ ማእቀፍ ላይ ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ

ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የድጋፍ ማእቀፍ ላይ ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ መንግሥት ብድሩን የሚያገኝበት ተከታታይ ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል። ቁልፍ ግዴታዎቹ ከስር የተዘረዘሩት ናቸው፡- 🟠 ቀጣይነት ያለው ቅድመ ሁኔታ፦ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ክፍያዎች ላይ የሚጣሉ ገደቦችን ማስወገድ፣ አንድ ወጥ የሆነ የምንዛሪ ስርዓትን ማስቀጠል እና “የተወሰኑ የሁለትዮሽ ክፍያ ስምምነቶችን” ከመግባት መቆጠብን ጨምሮ በተለዩ የፋይናንስ አሠራሮች መገዛት ይኖርበታል። ሆኖም አይኤምኤፍ ለአዲሷ የብሪክስ አባል ሀገር የተከለከሉ "የሁለትዮሽ ክፍያ ስምምነቶችን" አልገለጸም። 🟠 የህግ ማሻሻያ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአስተዳደር ማዘመን፣ የውሳኔ አሰጣጥን ማሳደግ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውስጥ ተጠያቂነትን እና ግልፅነትን ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ ረቂቅ የህግ ማሻሻያዎችን በታህሳስ 2024 መጨረሻ ለፓርላማው ማቅረብ ይጠበቅበታል። 🟠 በየደረጃው የሚፈጸም ክፍያ፦ የአፈጻጸም መስፈርቶች እና የአይኤምኤፍ ግምገማ በተሳካ ሁኔታ በሚጠናቀቅበት ወቅት የሚለቀቁ የተወሰኑ ክፍያዎችን በተመለከተ በአበዳሪ ድርጅቱ ሐሳብ ቀርቧል። የመጀመሪያው ክፍያ እ.አ.አ መስከረም 10፣ 2024 የሚፈጸም ሲሆን ተጨማሪ ክፍያዎች ቀጣይነት ባለው ተገዢነት ላይ ይመሰረታሉ። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመተግበር ላይ ስትሆን የሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሃና አርአያስላሴ ማሻሻያው ብዙ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ የሚያስችል "ትልቅ ለውጥ" ነው ሲሉ ገልጸውታል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0