የነሐሴ 14 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 14 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የናይጄሪያ ባለስልጣናት በኤምፖክስ ስርጭት ምክንያት ከፍተኛውን የስጋት ደረጃ እንዳወጁ አፍሪካ24 የቴሌቭዥን ጣቢያ ዘግቧል። 🟠 የመጀመሪያ ዙር የኤምፖክስ ክትባት በዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ በመጪው ሳምንታት እንደሚደርስ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ሳሙኤል ሮጀር ካምባ አስታውቀዋል። 🟠 በአፍሪካ አህጉር የወባ እና የዴንጊ ትኩሳትን ጨምሮ በወባ ትንኝ የሚተላለፉ በሽታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ከዓለም የወባ ትንኝ ቀን አስቀድመው ሳይንቲስቶች አስጠንቅቀዋል። 🟠 የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር የነዳጅ እና ጋዝ ውሎችን የሚገመግም እና ከብሔራዊ ጥቅም ጋር እንዲጣጣም ሃላፊነት የተጣለበት የህግ፣ ታክስ እና ኢነርጂ ባለሙያዎች ኮሚሽን ማቋቋማቸውን አስታውቀዋል። 🟠 ሁለት የዩክሬን ድሮኖች ክሬሚያ ላይ በአንድ ሌሊት እንደወደሙ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 በክሮከስ አዳራሽ የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች የእስር ጊዜያቸው እስከ ፈረንጆቹ ህዳር 22 እንዲራዘም በተላለፈው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ሳይጠይቁ ቀርተዋል። 🟠 ትራምፕ በምርጫ አሸናፊ የሚሆኑ ከሆነ ኤለን መስክ አማካሪ ሆኖ ማየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። 🟠 ካማላ ሃሪስ በፎክስ ኒውስ የክርክር መድረክ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ እንደቀሩ ትራምፕ ገለጹ። 🟠 የእስራኤል ጦር በሊባኖስ የሂዝቦላህ የሮኬት ክፍል ቁልፍ አባል የሆነውን ሁሴን አሊ ሁሴንን እንደገደለ አስታወቀ። 🟠 እስራኤል ሀማስ ዋሻዎችን እንዳይቆፍር ለመከላከል በጋዛ ሰርጥ እና ግብፅ መካከል ግንብ በመገንባት እቅዷ እንደጸናች እና በአከባቢው የሚገኙ ካሜራዎችን ልትቆጣጠር እንደሚገባ መግለጿን የአረብ አደራዳሪዎችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0