የነሐሴ 13 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ እና አዘርባጃን ፕሬዝዳንቶች ካካሄዱት ውይይት በኋላ በርካታ የጋራ ሰነዶችን ተፈራርመዋል። 🟠 ከኩርስክ ክልል ወረራ በኋላ ከኪዬቭ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር ሊኖር እንደማይችል የሩሲያው ፕሬዝዳንት በግልፅ ተናግረዋል ያሉት ላቭሮቭ ከኪዬቭ ጋር ለመነጋገር ግኑኝነት ተጀምሯል የሚሉ ሪፖርቶች ያልተረጋገጡ ወሬዎች ናቸው ብለዋል። 🟠 የዴንማርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃላፊ ዩክሬን የዴንማርክ ጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ የሩሲያን ግዛት ልታጠቃ እንደምትችል ተናግረዋል። 🟠 ሞስኮ ሩሲያ ላይ የጥላቻ መስመር በሚያራምዱ የብሪታኒያ የጥናት ተቋማት እና አማካሪ ኤጀንሲ ተወካዮች ላይ የግል ማዕቀብ እየጣለች እንደሆነ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በርሊን የኖርድ ስትሪም ፍንዳታን በተመለከተ ለሞስኮ መረጃ እየሰጠች ነው ቢልም የምርመራውን ጊዜያዊ ውጤት ግን ሳያሳውቅ ቀርቷል። 🟠 ሩሲያ የምዕራባውያን ጋዜጠኞች ወደ ግዛቷ በህገ-ወጥ መንገድ ሲገቡ እየመዘገበች እንደሆነ እና ህግ በጣሱት ላይ እርምጃ እንደምትወስድ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 "የብሪታንያ ቢል ጌትስ" እየተባለ የሚጠራው ባለብዙ ሚልየኔር ማይክ ሊንች በሲሲሊ የባህር ዳርቻ ከቱሪስቶች ጋር ይጓዝ የነበረበት መርከብ በመስጠሙ እንደጠፋ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የነሐሴ 13 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
የነሐሴ 13 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
Sputnik አፍሪካ
የነሐሴ 13 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ እና አዘርባጃን ፕሬዝዳንቶች ካካሄዱት ውይይት በኋላ በርካታ የጋራ ሰነዶችን ተፈራርመዋል። 🟠 ከኩርስክ ክልል ወረራ በኋላ ከኪዬቭ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር ሊኖር እንደማይችል የሩሲያው ፕሬዝዳንት... 19.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-19T20:06+0300
2024-08-19T20:06+0300
2024-08-19T20:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий