የሱዳን መንግሥት የልዑካን ቡድኑን ወደ ካይሮ ሊልክ እንደሆነ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
የሱዳን መንግሥት የልዑካን ቡድኑን ወደ ካይሮ ሊልክ እንደሆነ ተገለጸ ከአማፂያኑ ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ጋር ለ16 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም በስዊዘርላንድ እየተካሄደ በሚገኘው ድርድር እንደማይገኝ የገለጸው የሱዳን መንግሥት ከዚህ ቀደም የተደረሰውን የሰብዓዊ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ልዑካኑን ወደ ካይሮ እንደሚልክ አስታውቋል። ውሳኔው ከአሜሪካ እና ከግብፅ መንግስታት ጋር ከተደረገ ግጉኝነት በኋላ የመጣ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ከሁለቱም ወገኖች ጋር በተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማመቻቸት ጥረት በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ታውቋል። ገዢው የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት የካይሮ ልዑካን ቡድኑ ሲቪሊያኖችን ለመጠበቅ ባለፈው ዓመት በተደረሰው "የጅዳ ስምምነት አተገባበር ዙርያ የመንግሥት ራዕይ" ላይ እንደሚያተኩር አስታውቋል። የሰብዓዊ መርሆችን ማክበር እና የእርዳታ አቅርቦት ማድረሻ መስመር ክፍት ማድረግን የሚያካትተው የጅዳ ስምምነት በ2023 ግንቦት ወር ነበር የተፈረመው። ሆኖም የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ከሲቪል መኖሪያ ቤቶች እና ከህዝብ ተቋማት ለወውጣት የገባውን ግዴታ ለማክበር ፈቃደኛ ባለመሆኑ ጦርነቱ ቀጥሏል። የሱዳን መንግሥት፤ አደራዳሪዎች ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን ህጋዊ ለማድረግ እየሞከሩ በማለት በስዊዘርላንዱ ድርድር እንደማይሳተፍ ገልጿል። ሆኖም በሱዳን የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልእክተኛ ቶም ፔሬሎ በሁለቱ ወገኖች መካከል የበይነ መረብ ወይይቶች እንደቀጠሉ አረጋግጠዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0