በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ "በመንግሥት የጤና ላቦራቶሪ የተደረገው የውሃ ተቅማጥ ምርመራ ኮሌራ መሆኑን አረጋግጧል" ሲሉ የገለጹት የሱዳኑ የጤና ሚኒስትር ሃይታም ሞሀመድ ኢብራሂም፤ ከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት አረጋግጠዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በሱዳን 11,327 በኮሌራ የተያዙ ሰዎች እንደተመዘገቡ እና 316 የሚሆኑት መሞታቸውን ሪፖርት አድርጓል። በጦርነቱ ምክንያት የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ውስን እንደሆነ የገለጸው ድርጅቱ፤ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል አስጠንቅቋል። ወረርሽኙ ከሚያዝያ 2023 አጋማሽ ጀምሮ በሱዳን ጦር ኃይሎች እና በአማፂያኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች በምትገኘው ሱዳን የጨመረውን የጤና ቀውስ የሚያባብስ ነው። ጦርነቱ ከ16,650 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ አፈናቅሏል። ግጭቱ የጤና አገልግሎቶችን በማስተጓጎሉ ኮሌራ፣ ወባ፣ ኩፍኝ እና የደንጊ ትኩሳትን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎች እንዲስፋፉ አድርጓል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ
በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ "በመንግሥት የጤና ላቦራቶሪ የተደረገው የውሃ ተቅማጥ ምርመራ ኮሌራ መሆኑን አረጋግጧል" ሲሉ የገለጹት የሱዳኑ የጤና ሚኒስትር ሃይታም ሞሀመድ ኢብራሂም፤ ከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት... 18.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-18T16:48+0300
2024-08-18T16:48+0300
2024-08-18T17:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий