በቻድ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 265,000 የሚጠጉ ሰዎች ተጠቁ

ሰብስክራይብ
በቻድ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 265,000 የሚጠጉ ሰዎች ተጠቁ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (OCHA) እንዳስታወቀው ቻድ በምዕራብ እና ማእከላዊ አፍሪካ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ በከፍተኛ ደረጃ የተጠቃች ሀገር ነች። በአጠቃላይ በክልሉ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከ716,000 በላይ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን 62,000 የሚሆኑ ቤቶችን አውድሟል ወይም አፈራርሷል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለጻ በትንሹ 72 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 699 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። ቻድ 5,286 የተፈናቀሉ ሰዎችን በማስመዝገብ ከፍተኛ ቁጥር ተፈናቃዮች ከሚገኙባቸው ሀገሮች አንዷ ናት። በቀጠናው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ54,700 በላይ እንደሆነ ተገልጿል። "በ13 አውራጃዎች ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ አውሎ ንፋስ መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል፣ የእርሻ መሬት አጥለቅልቋል፣ ከብቶችን ጠራርጎ ወስዷል እንዲሁም አርባ ሰዎችን ገድሏል። በጣም አስቸኳይ ፍላጎቶች መጠለያ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች እና የምግብ ዕርዳታ ናቸው" ሲል የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ነሐሴ 1 ቀን በቻድ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በገመገመበት መግለጫው አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0