ዚምባብዌ የሳድክ የሊቀመንበርነት ቦታን በምስጋና ተረከበች

ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ የሳድክ የሊቀመንበርነት ቦታን በምስጋና ተረከበች የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የውጭ ሃይሎች ሀገራቸውን ለማግለል ግፊት ቢያደርጉም የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ መሪዎች ለሚሰጡት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና የማያወላውል አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል። ምናንጋግዋ በሃራሬ በተካሄደው የሳድክ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በአባል ሀገራት ላይ የሚደርሰውን “ያልተገባ ጫና” አንስተው ከዚምባቡዌ ጎን በመቆም ጽናታቸውን እንዳሳዩ አበክረው ተናግረዋል። "በአንዱ ላይ የሚደረስ ጉዳት በሁሉም ላይ የደረሰ ጉዳት ነው በሚለው የነጻነት ግዜ ትግል መፈክራችን እውነተኛ መንፈስ መሰረት በአቋማችሁ ጸንታችኋል" ብለዋል በንግግራቸው። "የሳድክ ክልል እንደሌሎች አንገብጋቢ የሰላም፣ የጸጥታ እና የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች ሁሉ በዚምባብዌ ዙርያ ያሳየው ግልፅነት፣ አብሮነት እና አንድነት በክልላችን መስራች አባቶች የታለመውን እውነተኛ የፓን አፍሪካ መንፈስ የገለጸ ነው።" ፕሬዝዳንቱ በተለይ ዚምባብዌ በመሬት ማሻሻያ ፖሊሲዋ ሳቢያ ላለፉት 24 ዓመታት በምዕራቡ ዓለም የአንድ ወገን ማዕቀብ ሲጫንባት ሳድክ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0