የሩሲያ ባለሙያዎች ስራ ለመጀመር እየተዘጋጀ ላለው የዚምባብዌ ብሔራዊ የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ስልጠና ሰጡ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ባለሙያዎች ስራ ለመጀመር እየተዘጋጀ ላለው የዚምባብዌ ብሔራዊ የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ስልጠና ሰጡ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ሩሲያውያን አብራሪዎች እና የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ለወደፊት የዚምባብዌ ስፔሻሊስቶች የመሳርያ አጠቃቀም ስልጠና ሲሰጡ ያሳያል። "ቡድናችን የዚምባብዌን ህዝብ በመርዳቱ ደስተኛ ነው። በአስጊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ህሙማንን ከገጠር አካባቢ ወደ ተሟሉ ሆስፒታሎች ማጓጓዝ እንችላለን" ሲል በሩሲያ የሄሊኮፕተር ኩባንያ ሄሊድራይቭ አብራሪ የሆነው አሌክሳንደር ሩሳኖቭ ተናግሯል። የዚምባቡዌ የጤና እና የህጻናት ጥበቃ ሚኒስትር ዳግላስ ሞምቤሾራ በበኩላቸው የመጀመሪያው የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ህሙማንን ለማከም የሚያስችሉ አስፈላጊ መሳሪያዎች የተሟሉላቸው ስድስት ሄሊኮፕተሮችን እንደሚያካትት ገልጸዋል። "የጤና ሰራተኞቻችንን አሰልጥነናል። አምቡላንሶቹን የሚያበሩ 20 የሚሆኑ ሰራተኞችን አሰልጥነናል ብለን እናስባለን። አብራሪዎቻችን በአሁኗ ሰዓት እየሰለጠኑ ይገኛሉ" ሲሉ ሞምቤሾራ አጠቃለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0