በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ17,500 በላይ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተመዘገበ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ተናገሩ "ከ2024 መጀመሪያ አንስቶ በ13 የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በአጠቃላይ 17,541 ሰዎች (2,822 የተረጋገጠ እና 14,719 የተጠረጠሩ) በኤምፖክስ መያዛቸውን እና 517 የሚሆኑት በቫይረሱ ምክንያት እንደሞቱ ተመዝግቧል" ሲሉ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ድረ-ገፅ ላይ በተለጠፈ መግለጫ አስታውቀዋል።ራማፎሳ በዚህ ሳምንት በሶስት ተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት ሀገራት ውስጥ በኤምፖክስ ቫይረስ እንደተያዙ የተጠረጠሩ ሰዎች እንደተመዘገቡ መጥቀሳቸውን ተከትሎም በህብረቱ ውስጥ ቫይረሱን ሪፖርት ያደረጉ ሀገራትን ቁጥር 16 አድርሶታል። ራማፎሳ ከ2023 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ2024 የኤምፖክስ ወረርሽኝ በ160% እንደጨመረ ጠቁመዋል። ከ2024 መጀመሪያ አንስቶ በሀገሪቱ ከ540 በላይ ሰዎች በኤምፖክስ ቫይረስ መሞታቸውን እና በተመሳሳይ ወቅት በበሽታው ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ 15,664 ሰዎች እንደተመዘገቡ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ሚኒስቴር ቀደም ሲል አስታውቋል። የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ወረርሽኙን ተከትሎ ቫይረሱ የአህጉሪቱ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ነው ሲል ያወጀ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት በመሰበስብ እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ17,500 በላይ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተመዘገበ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ17,500 በላይ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተመዘገበ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ17,500 በላይ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተመዘገበ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ተናገሩ "ከ2024 መጀመሪያ አንስቶ በ13 የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በአጠቃላይ 17,541 ሰዎች (2,822 የተረጋገጠ እና 14,719... 17.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-17T19:41+0300
2024-08-17T19:41+0300
2024-08-17T20:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በ13 የአፍሪካ ሀገራት ከ17,500 በላይ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተመዘገበ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
19:41 17.08.2024 (የተሻሻለ: 20:23 17.08.2024)
ሰብስክራይብ