ሩሲያ ለጊኒ ሪፐብሊክ 2 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለጊኒ ሪፐብሊክ 2 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ድጋፍ የተዘጋጀው የሰብዓዊ እርዳታ እርክክብ ስነ-ስርዓት ነሐሴ 10 ቀን በጊኒ የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ተካሂዷል። የስነ-ስርዓቱ ታዳሚዎች የተበረከተው ምግብ፤ 408.35 ሜትሪክ ቶን አተር እና 234.6 ሜትሪክ ቶን የሱፍ አበባ ዘይት፤ በጊዜያዊነት የተቀመጠበትን መጋዘንም ጎብኝተዋል። የቅድመ ዩኒቨርስቲ ትምህርት እና የመሰረታዊ ትምህርት ሚኒስትር ዣን ፖል ሴዲ የምግብ እርዳታው በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች እንደሚከፋፈል እና ራቅ ባሉ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የትምህርት ቤት ካፌዎች እንደሚላክ ተናግረዋል። እርዳታው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን፣ እርጉዝ እና ጡት አጥቢ እናቶችን እንዲሁም በኤድስ የተያዙ ሰዎችን ጨምሮ ከ84,000 የሚበልጡ ጊኒያውያንን እንደሚመለከት በጊኒ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ ሂዩንግ-ጁን ሊም አክለዋል። በኮናክሪ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሲ ፖፖቭ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የተለመደ ወዳጃዊ ግንኙነት አንስተዋል። ሩሲያ በአፍሪካ አህጉር የምግብ ዋስትና ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ ትኩረት እንደምትሰጥ እና በጣም ለተቸገሩ ሀገራት በየግዜው ነፃ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንደምታዘጋጅ አምባሳደሩ ጠቁመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0