በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ የምትገኘው ኢኳቶሪያል ጊኒ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች

ሰብስክራይብ
በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ የምትገኘው ኢኳቶሪያል ጊኒ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉዌማ ምባሶጎ ​​ለማኑዌል ኦሳ ንሱዊ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት "ውጤታማ አይደለም" ያሉት የቀድሞው መንግሥት የስራ መልቀቂያ ካስገባ ሶስት ሳምንታት በኋላ የመጣ ነው። ቦታውን በመያዝ የመጀመሪዋ ሴት የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌላ ሮካ ቦቴይ በፕሬዝዳንቱ ጥያቄ መሰረት ከተሾሙ 18 ወር በኋላ የስራ መልቀቂያቸውን በሐምሌ ወር አስገብተዋል። ምባሶጎ የስራ መልቀቂያው መንግሥት እንደ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ግኑኝነት እና ሙስና ያሉ ወሳኝ ጉዳዮችን መፍታት ባለመቻሉ የመጣ እንደሆነ ተናግረዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ የኢኳቶሪያል ጊኒ ብሔራዊ ባንክ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን "አስተዳደር የማስተባበር" ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0