ሴኔጋል የመጀመሪያውን ሳተላይት ወደ ህዋ በማምጠቅ የህዋ ዘመንን ተቀላቀች

ሰብስክራይብ
ሴኔጋል የመጀመሪያውን ሳተላይት ወደ ህዋ በማምጠቅ የህዋ ዘመንን ተቀላቀች ጌይንድሳት1-ኤ (GAINDESAT-1a) ሳተላይት ነሐሴ 10 ቀን በስፔስኤክስ ፋልኮን 9 ሮኬት ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ህዋ መጥቋል። የትራንስፖርተር 11 የጠፈር ተልዕኮ አካል የሆኑ ሌሎች 115 ትናንሽ ሳተላይቶችም በሮኬቱ ተጎጉዘዋል። ይህ "ለሀገራችን እድገት እና የጠፈር ሀገር የመሆን ፍላጎት ወሳኝ እርምጃ እና ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉ የሴኔጋል የጠፈር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ማራም ኬር ተናግረዋል። የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ሳተላይቱ "የመሐንዲሶቻችን እና ቴክኒሻኖቻችን የ5 ዓመታት ልፋት ፍሬ" ነው ሲሉ አወድሰውታል። "ይህ ስኬት ለቴክኖሎጂ ሉዓላዊነታችን ወሳኝ እርምጃ ነው" ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል። ጌይንድሳት1-ኤ ለምድር ምልከታ፣ ግንኙነት እና ሳይንሳዊ ምርምርን ጨምሮ ለተለያዩ ተግባራት ሊያገለግል ይችላል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0