ቡርኪናፋሶ በበርካታ የጸጥታ መስኮች በሩሲያ ድጋፍ ትተማመናለች የቡርኪናፋሶ መከላከያ ሚኒስትር ካሱም ኩሊባሊ ለሩሲያ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል "ሁለቱ ወገኖች በደንብ ይግባባሉ" ብለዋል። አፍሪካውያን የራሳቸውን ደህንነት መጠበቅ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሚኒስትሩ ከራሳቸው በስተቀር ማንም በተሻለ ሊሰራላቸው አይችልም ብለዋል። ሩሲያውያን ሊዋደቁላቸው የሚመጡ ከሆነ ቡርኪናፋሶውያን ችግር ይገጥማቸዋል ብለው እንደሚያምኑም አንስተዋል። ነገር ግን ሩሲያውያን የሚያቀርቡትን ማንኛውንም እውቀት እና መሳሪያ በደስታ ይቀበላሉ ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ሚኒስትሩ ምልከታ የሞስኮ አካሄዶች ከዚህ አስተሳሰብ ጋር የተጣጣሙ ናቸው። ካሱም ኩሊባሊ ከነሐሴ 6 እስከ 8 ድረስ በተካሄደው የአርሚ-2024 ወታደራዊ መድረክ ላይ ለመሳተፍ በሩሲያ ዋና ከተማ ተገኝተው ነበር። ከዝግጅቱ ጎን ለጎን ከሩሲያ አቻቸው አንድሬ ቤሎሶቭ ጋር ውይይት አድርገዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ቡርኪናፋሶ በበርካታ የጸጥታ መስኮች በሩሲያ ድጋፍ ትተማመናለች
ቡርኪናፋሶ በበርካታ የጸጥታ መስኮች በሩሲያ ድጋፍ ትተማመናለች
Sputnik አፍሪካ
ቡርኪናፋሶ በበርካታ የጸጥታ መስኮች በሩሲያ ድጋፍ ትተማመናለች የቡርኪናፋሶ መከላከያ ሚኒስትር ካሱም ኩሊባሊ ለሩሲያ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል "ሁለቱ ወገኖች በደንብ ይግባባሉ" ብለዋል። አፍሪካውያን የራሳቸውን ደህንነት መጠበቅ እንዳለባቸው አጽንኦት... 17.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-17T15:39+0300
2024-08-17T15:39+0300
2024-08-17T16:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий