የነሐሴ 10 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 የዩክሬን ጦር በሩሲያ ዶንየትስክ በሚገኘው "ጋላክትካ" የገበያ ማዕከል ላይ ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 11 ቆስለዋል። 🟠 ፑቲን ከሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ጋር ስብሰባ አድርገዋል፤ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ወቅት ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚገቡ አዳዲስ ቴክኒካዊ መፍትሄዎች ዙሪያ በመወያየት ሀሳብ አቅርበዋል።🟠 ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሩሲያ ኩርስክ ክልል ነዋሪዎች፤ ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ህጻናትን ጨምሮ በ19 የሩሲያ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ 153 ጊዜያዊ የመጠለያ ማዕከላት እንዲዘዋወሩ መደረጉን የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ሚኒስቴር አስታወቀ።🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ በክራይሚያ ድልድይ ላይ ያነጣጠሩ 12 ATACMS ሚሳኤሎችን በመጥለፍ ማውደሙን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 በእስራኤል እና በኢራን መካከል መጠነ ሰፊ ጦርነት መኖሩ የማይቀር ነው ሲሉ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናግረዋል።🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ ብራንድ መጽሐፍ ቅዱሶችን በመሸጥ 300,000 ዶላር ገቢ ማግኘታቸውን የባንክ ሒሳብ መግለጫዎችን ዋቢ በማድረግ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የነሐሴ 10 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች
የነሐሴ 10 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የነሐሴ 10 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 የዩክሬን ጦር በሩሲያ ዶንየትስክ በሚገኘው "ጋላክትካ" የገበያ ማዕከል ላይ ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 11 ቆስለዋል። 🟠 ፑቲን ከሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ጋር ስብሰባ አድርገዋል፤ በዩክሬን ልዩ... 16.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-16T20:30+0300
2024-08-16T20:30+0300
2024-08-16T20:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий