የነሐሴ 10 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 10 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ሰራዊት በጥቁር ባህር ላይ 5 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ ማውደሙን የገለፀ ሲሆን፤ በተጨማሪ ወደ ክራይሚያ የሚሄዱ ሁለት ሰው አልባ ጀልባዎችንም ማውደሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 በሩሲያ የኩርስክ ግዛት ላይ የተፈፀመው ጥቃት የዩክሬን ጦር በምስራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳያባብስ ስጋት መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።🟠 ኤፍቢአይ የሩሲያ ተወላጅ የሆነውን አሜሪካዊ የፖለቲካ ሳይንቲስት ዲሚትሪ ሲምስን ቤት ፈተሸ።🟠 የአሜሪካ ደህንነት አገልግሎት የትራምፕን ደህንነት ለመጠበቅ የተወሰኑ የባይደን የደህንነት አባሎችን መላኩን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።🟠 ትራምፕ በምርጫው ካሸነፉ አሜሪካ ከኢራን ጋር "ወዳጅ" እንደምትሆን ቃል ገብተዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0