ቱርክ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ የከፈታቸውን ክስ ለመቀላቀል መወሰኗን ፍልስጤም በደስታ እንደምትቀበለው ማሃሙድ አባስ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ቱርክ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ የከፈታቸውን ክስ ለመቀላቀል መወሰኗን ፍልስጤም በደስታ እንደምትቀበለው ማሃሙድ አባስ ተናገሩ"በፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የሚመራውን የቱርክ አመራር እናደንቃለን። ደቡብ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ፍርድ ቤት እስራኤል ላይ የከፈተችውን ክስ ቱርክ መቀላቀሏን በደስታ እንቀበላለን። " ቱርክ ለፍልስጤም ያላትን አጋርነት ለማሳየት ከእስራኤል ጋር ያላትን 10 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የንግድ ስምምነት ማቋረጧንም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ለቱርክ ፓርላማ ባደርጉት ንግግር ላይ ተናግረዋል።አባስ ለቱርክ ፓርላማ አባላት ንግግር ለማድረግ ትናንትናው ረቡዕ ማምሻውን አንካራ ገብተዋል። በቱርክ ፓርላማ አካባቢ የደህንነት እርምጃዎች ተጠናክረው የነበሩ ሲሆን ጋዜጠኞች ሁለት ዙር  ፍተሻ ካደረጉ በኋላ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፤ በፓርላማው ህንፃ ዙሪያ ፎቶግራፍ ማንሳት ግን የተከለከለ ነው።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0