ቻድ በምዕራብ ሳሃራ ቆንስላ ፅህፈት ቤቷን ከፈተች

ሰብስክራይብ
ቻድ በምዕራብ ሳሃራ ቆንስላ ፅህፈት ቤቷን ከፈተች ከአልጄሪያ ባለስልጣናት በኩል እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።እስካሁን ድረስ ወደ 29 የሚጠጉ ሀገራት ቆንስላ ፅህፈት ቤቶቻቸውን በምእራብ ሰሃራ በላዮዩን እና ዳክላ ከተማ የከፈቱ ሲሆን፤ እንደ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኮትዲቯር፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ቡሩንዲ ያሉ የአፍሪካ ሀገራትንም የቆንስላ ፅህፈት ቤታቸውን አቋቁመዋል።ቀደም ሲል የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረችው ምዕራብ ሳሃራ በ1975 በሞሮኮ እና በሞሪታኒያ አስተዳደር ስር ወደቀች። እ.ኤ.አ በ1976 የፖሊሳሪዮ ግንባር የተሰኘው የአካባቢው ብሄርተኛ ቡድን የሳህራዊ አረብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን አወጀ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአልጄሪያ የሚደገፈው የፖሊሳሪዮ ግንባር ከሞሮኮ ጋር አካባቢውን ለመቆጣጠር ግጭት ውስጥ ገብቷል። በአሁኑ ጊዜ ሞሮኮ 80% የሚሆነውን የምእራብ ሰሃራን ግዛት ታስተዳድራለች፣ የፖሊሳሪዮ ግንባር ደግሞ ቀሪውን 20% ይቆጣጠራል።ፎቶ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ነውስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0